Education
አና ወደ በርሊን 1989 ዓ ም ፤ በግንቡ መፍረስ የተነሳ ትልቅ ደስታ ወደሚታይበት ከተማ ትመለሳለች። በዚህ ግርግር ተጋፍታ ማህደሩን መውሰድ አለባት። ይሳካላት ይሆን? ልክ አና ወደ 1989 ዓ ም ልትጓዝ ስትል ጥቁር ኮፍያ የሚያደርጉት ብቅ ይላሉ። ቀይ ለባሿ ሴት አናን እንዲፈልጉ ትዕዛዝ ትሰጣለች። በህይወት እንዲያመጧት! አና ግን የድሮውን ነገር በሚያስታውሰውን ነገር በሰዐቷ የበርሊን ግንብ ወደ ፈረሰበት ቀን ትመለሳለች። የብራንድቡርገር በር ጋር ግርግር ውስጥ ቆማለች። ግን ወደ በርንአወር መንገድ መሄድ አለባት። 30 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የቀሯት። ግን ከዚህ ግርግር በሰዐቷ ተከፋፍላ ከነበረችው ከተማ መውጣት ትችል ይሆን?