Education
አና አሁንም የእንቆቅልሹን መልስ አልደረሰችነትም። RATAVA የትኛውን ክስተት ሊያሰናክል ይፈልጋል? አና ወደ 2006 ዓ ም ከተመለሰች በኋላ ወደ 1989 መጓዝ አለባት። ግን ጉዞው ምን ያህል አደገኛ ነው? አና ወደ 2006 ዓ ም ከመመለሷ በፊት ከፓውል ጋር በደስታ ትሰናበታለች። 35 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው አላማውን ለማሳካት የሚቀሯት? ተጫዋቹና አና አሁንም የእንቆቅልሹን መልስ ለማግኘት ይሞክራሉ። ለምሰሌ RATAVA የትኛውን ታሪካዊ ክስተት ሊያሰናክል እንደሚፈልግ። ወዲያው ሽብር ፈጣሪዎቹ የግንቡ ግንባታ ሳይሆን የግንቡን መፍረስ አንደሚፈልጉ ይደርሱበታል። ተጫዋቹ ወዲያው አና ወደ 1989 ዓ ም እንድትጓዝ ይወስናል። ግንቡ ሲፍረስ አና በቦታው እንድትገኝ።