Mission Berlin 17 – የአጥር ግንባታ

Share:

Listens: 0

Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

Education


50 ደቂቃዋች ይቀራሉ። ተጫዋቹ ገንዘብ ተቀባይዋን ማመን እንደሚሻል በሙሉ ሀላፊነት ይወስናል። በሬድዮ ምስራቅ ጀርመን አጥሩ ጋር ስለቆሙ ወታደሮች ይወራል። ይኼ የ RATAVA መልስ ይሆን? አና እስካሁን ገነዘብ ተቀባይዋ ሀይድሩን ድራይ እንደሆነች አላወቀችም። ተጫዋቹ ለርዳታ ፍቃደኛ የሆነችውን ሴት ምንም እንኳን ወንድሟ ፓውል አጠራጣሪ ቢሆንም አና እንድታምናት ይመክራታል። ሆኖም እሱ አና ሞተር ሳይክል ነጂዎቹን እንድታመልጥ እንደሚረዳ ፍቃደኛ ይሆናል። በኋላም አና ፤ፓውልና ሀይድሩን የምስራቅ ጀርመን ወታደሮች እንዴት የሚዋጋ ሽቦ መንገድ ላይ እንደሚያስቀምጡ ያያሉ። ተጫዋቹ አናን የግንብ ግንባታው ስራ ማስጀመሪያ እንደሆነ ይነግራታል። አና ጀርመንን ለማዳን 45 ደቂቃዋች ብቻ ናቸው የቀሯት።