Education
በ 1961 ኛው ዓ ም አናን የታጠቁት ሞተር ሳይክል ነጂዋች ያባርሯታል። በዚህ አስፈሪ ጊዜ አንዲት የማትታወቅ ሴት ትረዳታለች። ግን ለምን ትረዳታለች? አናስ ልታምናት ይገባል? ሞተር ሳይክል ነጂዎቹ አናን ይከታተሏታል። እሷም ወደ ምግብ መሸጫ መደብር እሸሻለች። የሱቁ አለቃ እየዘጋ እንደሆነ ሲነግራት አንዷ ተቀጣሪ አና ጓደኛዬ ነች ትላለች። ገነዘብ ተቀባይዋ አናን ወደ ቤቷ ትወስድና የ ት/ ቤት ጓደኛዋ ነኝ ትላለች። አና ትጠራጠራለች ግን ተጫዋቹ አና ሴትዬዋን ማመን እንዳለባት ይነግራታል። አና የ ገነዘብ ተቀባይዋ ቤት የሴትየዋን ወንድም ፓውል ቪንክለር ትተዋወቃለች።