Mission Berlin 15 – የጊዜ ጉዞ

Share:

Listens: 0

Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

Education


አና ከተከፈለችው ምስራቅ በርሊን ወደ ምዕራብ በርሊን መመለስ አለባት። ግን ይህ ብቻ አይደለም። በ 55 ደቂቃዎች ውስጥ RATAVA ምን እንደሆነ ጭምር፤ የበርሊን ግንብ ምስረታ ወይስ ፍርስ? አና 1961 ኛው ዓ ም እንደደረሰች ወደ ካንት መንገድ ለመሄድ ትሞክራለች። ይህ ግን ሊሳካ አይችልም። ምክንያቱም የDDR መንግስት የግንብ ግንባታውን ስለጀመረና አና ደግሞ በምስራቁ በኩል ስላለች። ግን የካንት መንገድ ምዕራብ በርሊን ነው የሚገኘው። ጨዋታውን እንደ አዲስ ካደሱ በኋላ አናና ተጫዋቹ ሁለት ታሪካዊ ክስተቶች ያገኛሉ፦ የ RATAVA አላማ ሊሆን የሚችሉ። የበርሊን ግንብ ምስረታ ወይስ ፍርሰት። ተጫዋቹና አና ይህንን ለማወቅ 55 ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚቀራቸው።