Mission Berlin 13 – የእግዚያብሄር እርዳታ

Share:

Listens: 0

Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

Education


ቤተ ክርስትያኒትቱ መረጃ ለመሰብሰብ ትክክለኛ ቦታ ሳትሆን አትቀርም። ቄሱ ለአና የሙዚቃው ቅንብር የድሮውን ነገር የሚያስታውስ ቁልፍ እንደሆነ ያብራራላታል።ግን ምን አይነት መሳሪያ ማለቱ ነው? ጨዋታው እንደ አዲስ ከተጀመረ በኋላ አና ከቀይ ለባሿ ሴት ታመልጣለች። ቄሱ ለአና መርማሪ ኦጉር እንደቆሰለና ሆስፒታል እንደተኛ ይነግራታል። ለአናም የሙዚቃውን ቅንብር በድጋሚ ያሰማትና የሙዚቃው ኖት አደራደር D A C H F E G የድሮውን ነገር የሚያስታውሰን ቁልፍ እንደሆነ ያብራራላታል። ይኼ ድል ለተጫዋቹና ለአና የአስር ደቂቃዎች ሽልማት ያስገኛቸዋል። ግን ጊዜው ይበቃቸው ይሆን?