Education
አና 65 ደቂቃዎች ይቀሯታል። የመጫወቻው ቀፎ የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን አካል መሆኑን ትደርስበታለች። ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ከአና ቁልፍ ትጠይቃለች። ግን ምን አይነት ቁልፍ? የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን ከመጫወቻው ቀፎ ጋር አንድ አይነት የሙዚቃ ቅንብር ይጫወታል። አና ቀረብ ብላ የቤተክርስትያን አገልጋዩ ለጎብኝዎች የሚለውን ታዳምጣለች። ኦርጋኑ መታደሱን፤ የበርሊኑ ግንብ ከተሰራ በኋላ ግን ኦርጋኑ አንድ አካል እንደሚጎለው ይናገራል። አና የመጫወቻው ቀፎ የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን አካል መሆኑን ይገባታል። ኦርጋኑ መጫወት ሲጀምር አንድ በር ይከፈትና ቀይ ለባሿ ሴት ፊት ለፊቷ ትቆማለች። አና አንዱን ህይወቷን ታጣለች። የቀራትም 60 ደቂቃዎች ብቻ ነው።